የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ክላስተር ማዕከል ላይ የግቢ አጥር ግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ክላስተር ማዕከል ላይ የግቢ አጥር ግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ ተጫራቾች በሚከተሉት መመዘኛዎች መሠረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡
1. ተፈላጊ መመዘኛዎች
• የሥራ ዘርፉ የሕንፃ ግንባታ (BC) ወይም አጠቃላይ ግንባታ (GC) ሆኖ ደረጃ 7 (Grade 7) እና ከዚያ በታች የሆነ ብቻ
• በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው።
• የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 1) ያለው፡፡
• የቅርብ ጊዜ የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance) እና በመንግሥት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ የሚችል።
2. የግንባታው ዝርዝር ይዘት
• የግንባታው ቦታ፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ካፋ ዞን፣ ቦንጋ ከተማ።
• የሥራው ዓይነት፡ የግቢ አጥር ግንባታ፡፡
3. የጨረታ ሰነድ አገዛዝ እና አቀራረብ
ተጫራቾች የማይመለስ ብር [300 (ሶስት መቶ ብር)] በቢሮ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000705389137 ላይ ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ከቢሮአችን በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት የግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) መጠን ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የጨረታ ሰነዱ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ) በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መግባት ይኖርበታል።
4. ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ጊዜ
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል። ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ፣ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን በ 4፡30 ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ክፍል ይከፈታል። (22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል)።
ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡
ስልክ፡ [+251 912 932 500]
አድራሻ፡ ቴፒ
የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ
