Tender Detail

Tender Details

  • Company የአብክመ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ
  • Address , Phone: 0334319805
  • Website
  • Deadline07 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-07 00:00:00
  • Categories Construction Works

የአብክመ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ የተለያዩ የግንባታ ሥራዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

የአብክመ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ


በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የአብክመ ህ/ጤ. አ/ወ/ቅ/ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 002/2018

 

የአብክመ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ የተለያዩ የግንባታ ሥራዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.       የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2.       የግብር መክፈያ ቁጥር /ቲን ነበር/ ያላቸው፤ ግዥው ከ200000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና ማቅረብ የሚችል።

3.       ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፤ ፊርማና ስም በሚነበብ መልኩ መጻፍና በየገጹ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል።

4.       ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም የመንግሥት ግብር እና ታክስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት።

5.       ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6.       ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ ወይም በሌሎች መሆኑ ታውቆ ሁሉንም መሙላት አለባቸው።

7.       ተጫራች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ በውሉ መሠረት መፈጸም አለበት።

8.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአብክመ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ/ ብር በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።

9.       የጨረታ ሳጥኑ በ22ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10.   በጨረታው ያልተገኙ ተጫራች ፖስታው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሠረት ተገዥ ይሆናል፡፡

11.   ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜው ከ5 ቀን በፊት ለኢንስቲትዩቱ ቅርንጫፍ ማሳወቅ አለበት።

12.   የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ በመሂ ፣ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ ኦርጅናሉን በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚፃፍ ሲፒኦ ወይም ሌሎች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶች ጋራንታቸው ከ3/ሦስት/ ወር ወይም 90 ቀን ማነስ የለበትም።

13.   የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

14.   የተሳሳተ ስርዝ ድልዝ/ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።

15.   መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16.   ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።

17.   የግንባታ ሥራ ግዥ ደረጃ 6 GC እና በላይ ተቋራጮች መሆን አለባቸው።

ማሳሰቢያ፡-

ተጫራቾች ስበስጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0334319805 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

 

የአብክመ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ

Save Tender