Tender Detail

Tender Details

  • Company ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline21 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-21 00:00:00
  • Categories Personal Protective Safety Equipment

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኢማ ለድርጅቱ አሽከርካሪዎች ደኅንነት መጠበቂያ አስፈላጊ የመከላከያ መሣሪያዎችን (Drivers essential protective equipment's) የሆኑ የራስ ቆብ (Helmet) አንፀባራቂ ሰደሪያዎች (high visibility safety vests) ፣ ሴፍቲ ጫማዎች (safety shoes) እና የመጀመሪያ ርዳታ መስጫ (first aid kit) በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶ

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/09/2018

 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኢማ ለድርጅቱ አሽከርካሪዎች ደኅንነት መጠበቂያ አስፈላጊ የመከላከያ መሣሪያዎችን (Drivers essential protective equipment's) የሆኑ የራስ ቆብ (Helmet) አንፀባራቂ ሰደሪያዎች (high visibility safety vests) ፣ ሴፍቲ ጫማዎች (safety shoes) እና የመጀመሪያ ርዳታ መስጫ (first aid kit) በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ፡-

1.       በዘርፉ የተሰማሩ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና ሌሎች አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

2.       ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ሕንፃ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።

3.       ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈረም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል።

4.       ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

5.       የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።

6.       ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም።

7.       በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።

8.       በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም።

9.       ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል።

10.   ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

11.   የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

12.   ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ: - ሰንጋ ተራ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ሕንጻ 12ኛ ፎቅ

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ

Save Tender