Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
  • Address ደሴ በሚገኘው በጥገና ጽ/ቤቱ ግዥና ፋ/ን/አ/ደ/ ስራ ሂደት ቢሮ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-11-62-29
  • Website
  • Deadline31 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-31 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ለጥገና ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ አንድ ከ24 ሰው ጀምሮ ከዛ በላይ ተሳፋሪ የሚይዝ የህዝብ መጓጓዥያ ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል።

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ለጥገና ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ አንድ ከ24 ሰው ጀምሮ ከዛ በላይ ተሳፋሪ የሚይዝ የህዝብ መጓጓዥያ ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ከዚህ በታች ሊሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

1.     ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆነዎ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላቸው አንዲሳተፉ ይፈልጋል።

2.     ተጫራቾች ሰነዱ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ከ 7/7/2018 እስከ 21/7/08 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ደሴ በሚገኘው በጥገና ጽ/ቤቱ ግዥ/ፋ/ን/አ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያውን የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ለመ/ቤቱ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

4.     ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆንዎ የሚያረጋግጥ የዋናውን ፎቶ ኮፒ በማያያዝ በፖስታ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በጥገና ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

5.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ካወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታና በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የድርጅትዎን ማህተምና አድራሻ ፊርማ በማድረግ ለመስሪያ ቤቱ ማቅረብ አለባቸው።

6.     ጨረታው 22/7/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ የተሟላ ከሆነ ያከፈታል።

7.     አሸናፊ ተጫራች ከታወቀ በኋላ ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 10% የተረጋገጠ ቼከ /ሲፒኦ/ ለመ/ቤቱ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

8.     ተሸናፊ ተጫራች ያስያዙት ቼክ /ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

9.     ጥገና ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው በመሰረዙ ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ያወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ ከሰአት እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።

11. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ

 

በፋክስ ቁጥር 033-111-44-23 በመላክ ወይም

ስልክ ቁጥር 0331116229

 

በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት

Save Tender