በሀዲያ ዞን የሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአጥር ግንባታ ሥራ ለማሰራት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
Shone Tvet College (የሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዲያ ዞን የሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአጥር ግንባታ ሥራ ለማሰራት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ደረጃቸው BC-6/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ግዥ ፋይ/ን) አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 500 /እምስት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካይ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በማስያዝ መግዛት ይችላል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኞችን አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል በሁለት ፎቶ ግራፍ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በስም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱን ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በስም አሽጐና የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ የቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶግራፍ ከኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሂሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በስም በታሽገ ፖስታ በማድረግ አራቱን የቴክኒካል ሰነዶች በሌላ ማጠቃለያ ፖስታ በስም አሽጐ ሁለቱንም የቴክኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ ፖስታ በማድረግ የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የአገልግሎት ዋጋው በሰነድ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሀዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጂናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) መጠይቆቹ (ባዶ ቦታዎች) ላይ ሳይሞሉ እና ሳይፈርሙ ማህተም ብቻ አድርጐ መመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል::
4. ጨረታው በ31ኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ አሰሪው መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡
• የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የግዢ መመሪያ 36/2018 ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
• ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ገበያ ዋጋ በታች ያቀረበ እንደሆነ አሰሪው መ/ቤት ውል ለመግባት አይገደድም።
• ለአሰሪው መ/ቤት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር ከአጠቃላይ የሥራ መጠን 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ውል መግባት ይችላል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912119049/0902450801 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ /ሾኔ/
