የቦንጋ ማረሚያ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት ለመንግሥት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒዩተር /የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ፖሊስ የቦንጋ ማረሚያ ተቋም
የጨረታ ማስታወቂያ
የቦንጋ ማረሚያ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት ለመንግሥት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ
1ኛ. ኮምፒዩተር /የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
2ኛ. ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል
ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ነጋዴዎች/በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች፡-
1ኛ. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
• በዘርፉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
• በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የዘመኑን የመንግሥት ግብር በመከፈል ንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ሆኖ ኦርጅናል ንግድ ፈቃድ አቅርቦ ማመሳከር የሚችል፡፡
2ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ CPO/ ማስያዝ የሚችል፣፣
3ኛ. የውል ማስከበሪያ ብር 50,000.00/ ሃምሳ ሺህ ብር/ CPO/ ማስያዝ የሚችል፡፡
4ኛ. በራሱ ትራንስፖርት እስከ ማረሚያ ተቋም ቅጥር ግቢ ማድረስ የሚችል፡፡
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ መግዛት ይችላሉ።
• ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት ዋጋ ገልጸው በታሸገ ፖስታ እስከ 15ኛ የሥራ ቀናት ድረስ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
• ጨረታው በ16ኛ ቀን እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በማረሚያ ግቢ ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
• ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
• የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
የቦንጋ ማረሚያ ተቋም
