Tender Detail

Tender Details


በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት በቤንች ሸኮ ዞን በሼ/ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በወረዳችን ውስጥ በሚገኘው ባታ የካሹ ድልድይ ግንባታ ተጨማሪ ሥራዎች ከዚህ ቀደም በነበረው የግንባታ ውል ላይ ያልነበሩ ለአፈር መከላከያ የሚያስፈልጉ እና ለመንገድ ሙሊት ስራ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/ሕ/ መንግስት በቤንች ሸኮ ዞን በሼ/ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት በቤንች ሸኮ ዞን በሼ/ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በወረዳችን ውስጥ በሚገኘው ባታ የካሹ ድልድይ ግንባታ ተጨማሪ ሥራዎች ከዚህ ቀደም በነበረው የግንባታ ውል ላይ ያልነበሩ ለአፈር መከላከያ የሚያስፈልጉ እና ለመንገድ ሙሊት ስራ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ማቅረብ የሚገባቸው

1.     ደረጃ 7 Gc እና ከዚያ በላይ

2.     ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ 2018 በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የቫት ተመዝጋቢነት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ፣ እና ታክስ ክሪላንስ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 500 ብር አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሼቤ/ወ/ገ/ጽ/ቤት መግዛት ይጠበቅበታል፡፡

3.     የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /አምሳ ሺ ብር/በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ከሰነድ ጋር ማስያዝ አለበት፤

4.     አሸናፊው ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10% በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቼከ ወይም ጥሬ ገንዘብ ዋስትና በማስያዝ ውል መግባት የሚችል መሆን አለበት፤

5.     ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ / ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማሳረፍ ማቅረብ አለባቸው፤

6.     ተጫራቾቹ በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾቹ ህጋዊ ወኪል ፊርማና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡

7.     በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ ፤ አድራሻና የድርጅቱ /የተወካዩን/ ስልክ ቁጥር በመግለጽ መፃፍ አለባቸው፡፡

8.     ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የ 1 ኦርጂናልና 2 ኮፒ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፤ የጨረታው ሰነድ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 90 ቀናት ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ 28 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡

9.     ጨረታው በ16ኛው ቀን በሼ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ስራ ቀን ይከፈታል፡፡

10.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

11.  አሸናፊው ተጫራችያሸነፈበት ስራውል መግባትይጠበቅበታል፤ በተጨማሪም ያሸነፈበት የግንባታ ስራዎች በሚሰሩበት ቦታ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡

12.  የግንባታው አድራሻ በሼ/ቤ/ወ/ባታ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0917161765/0917972404

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/ሕ/ መንግስት በቤንች ሸኮ ዞን  በሼ/ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

Save Tender