Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል
  • Address , Phone: 0115256823
  • Website
  • Deadline22 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-22 00:00:00
  • Categories Equipment And Accessories , Equipment

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል፡

➢  ሎት 1) የጥገና ዕቃዎች (የህንፃ መሳሪያ የኤሌክትሪክ የቧንቧና የመጸዳጃ ቤት ዕቃዎች)

➢  ሎት 2) ህትመት

➢  ሎት 3) የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች

➢  ሎት 4) መድሃኒት የላብራቶሪ ሬኤጀንትና የህክምና ዕቃዎች

➢  ሎት5) የማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤት የተለያዩ መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያ ዕቃዎች

➢  ሎት 6) የማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤት የህፃናት ወተት

➢  ሎት 7) የማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤት ህፃናት ዳይፐር፣ ሌሎች የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች

የአዋቂ የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎችና ኮስሞቲክስ ዕቃዎች

➢  ሎት 8) የአይሲቲ ዕቃዎች

➢  ሎት 9) የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች

➢  ሎት 10) የላውንደሪ ማሽን

➢  ሎት 11) የጉድጓድ ውሃ for demobilization, well rehabilitation and pump reinstallation የጥገና ስራ

➢  ሎት 12) የምግብ አቅርቦት ለአንድ ዓመት

➢  ሎት13) የፅዳት አገልግሎት ለአንድ ዓመት

➢  ሎት14) የኦክስጅን አቅርቦት ለአንድ ዓመት

➢  ሎት15) የበረኪና አቅርቦት ለአንድ ዓመት የሚያቀርቡለትና የሚሰሩለት ድርጅቶች

ይፈልጋል በመሆኑም፣ ከላይ ለተጠቀሰው የሚቀርቡ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

1.       ከሚያቀርቡት እቃ ጋር የተዛመደ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፤ የVAT፣ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገለፅ ማስረጃ በግልፅ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

2.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ሰነዱን ሆስፒታሉ ግቢ በሚገኘው የመንግስት ሂሳብ እና ክፍያ ደጋፊ የስራ ሃደት በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

3.       ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ሎት1) ለጥገና ዕቃዎች (የህንፃ መሳሪያ፣ የኤሌክትሪክ፣ የቧንቧና የመጸደጃ ቤት ዕቃዎች)

➢   ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፤ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 2 ለህትመት ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ) በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 3) ለፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 4 ለመድኃኒት፣ የላብራቶሪ ሬኤጀንትና የህክምና ዕቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 5) ለማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤት የተለያዩ መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያ ዕቃዎች ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ )በጥሬ ገንዘብ፤ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት6) ለማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤት የህፃናት ወተት ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 7) ለማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤት የህፃናት ዳይፐር ፣ ሌሎች የንፅህና መጠበቂያዕቃዎች የአዋቂ የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎችና ኮስሞቲክስ ዕቃዎች ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 8) ለአይሲቲ ዕቃዎች ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 9) ለመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 5000.00 (አምስት ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት) 10 ለላውንደሪ ማሽን ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 11) ለጉድጓድ ውሃ for demobilization, well rehabilitation and pump reinstallation የጥገና ስራ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 12) ለምግብ አቅርቦት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 13) ለፅዳት አገልግሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 14) ለኦክስጅን አቅርቦት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና

➢  ሎት 15) ለበረኪና አቅርቦት ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመግለጽ አንድ ኦሪጅናል ፋይናንሻል፤ አንድ ኦሪጅናል ቴክኒካል አንድ ኮፒ ፋይናንሻል አንድ ኮፒ ቴከኒካል በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ሆስፒታሉ ባዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ማስገባት ይኖርባቸዋል።

➢  ተጫራቹ ወደ ጨረታው ሳጥን ፖስታውን ሲያስገባ ቴክኒካል ለብቻ ፋይናንሻል ለብቻ መሆን አለበት። ይህ ሳይሆን ቢቀር እና ተጫራቹ ፋይናንሻሉ እና ቴክኒካሉን በአንድፖስታ ካስገባ ጨረታው ወዲያውን ወድቅ ይሆንበታል።

4.       ጨረታው በሚያበቃበት የመጨረሻ ቀን (በአስራ አንደኛው ቀን) ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ በ4:30 በሆስፒታሉ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5.       የበለጠ መረጃ ቢያስፈልገዎት በስልክ ቁፕር፡- 011 525 6823 ደውለው ይጠይቁ።

6.       ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል

Save Tender