Tender Detail

Tender Details

  • Company Central Ethiopia regional state justice Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ)
  • Address ሀላባ ቁሊቶ ከተማ : ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046556250-
  • Websitehttps://www.cerjustice.gov.et/
  • Deadline23 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-24 00:00:00
  • Categories Generators

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ጄኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Central Ethiopia regional state justice Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ጄኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1.     በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

3.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡

4.     የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመስሪያ ቤቱ ግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት በነጻ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5.     ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በማካተት የቴክኒክና የፋይናሻል ሰነዳችሁ በሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ /ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6.     የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ላይ ይታሸግና በ11ኛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡

7.     ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡

8.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0465562550 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ግዢ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት

ሀላባ ቁሊቶ

Save Tender