የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር በሚገኘው ቢሯችን እና ኮምኮልቻ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚገኙትን ያገለገለ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Water Works Construction Enterprise (WWCE) (የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ሽያጭ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ግ/ጨ/ቁጥር 47/2018
የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር በሚገኘው ቢሯችን እና ኮምኮልቻ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚገኙትን ያገለገለ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች የሚሸጡትን ያገለገለ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች፣ ዋናው መ/ቤት ፕላስቲክ ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ስቶር፣ ኮምቦልቻ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሚገኘው በአካል በመገኘት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት በመመልከት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይቻላል፡፡
2. በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆነ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በማህበር ለመወዳደር የሚፈልግ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ በፍትህ ተቋም የተሰጠውን ሕጋዊ ውከልና ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚኘው ቢሯችን ቢሮ ቁጥር 02 ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ሠዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /bid bond/ የተጨማሪ እሴት ታክስን 15% ጨምሮ የሚገዙበትን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በባንክ ማስያዥያ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክ እንደማስያዥያ ማቅረብ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልከ ከ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙትን የጨረታ ማስያዣ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል፡፡
7. አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በከፈሉ ማግስት ጀምሮ እቃውን በ15 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን በተባለው ቀን የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት ሲፒኦ ተወርሶ ኮርፖሬሽኑ የሚያዋጣው ከሆነ 2ኛ ለወጣው ተጫራች የሚሸጠው ይሆናል፡፡
8. ጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ከ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን፣ በኮምቦልቻ በሚገኘው ቢሯችን እንዲሁም በአዲስ አበባ በሚገኘው ቢሯችን ከሳሪስ ዳማ ሆቴል ፊት ለፊት ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000265163223 አስገብተው ማስረጃ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።
9. ገዥው በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ እቃውን መረከብ ባይችል ያጋጠመውን ችግር ከበቂ ማስረጃ ጋር በጽሑፍ አመልክቶ የድርጅቱ የሚመለከተው ኃላፊ ሲፈቅድ ብቻ የርክክብ ጊዜው ሊራዘም ይችላል፡፡
10. የሚሸጡት ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችንና ማሽነሪዎችን በተመለከተ የሚኖር ማንኛውንም ወጭ በአሸናፊው የሚሸፈን በመሆኑ በዚህ አግባብ ግዴታ የሚገባ ይሆናል፡፡
11. ለእያንዳንዱ እቃ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል፡፡
12. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም፡፡ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ :- በስልክ ቁጥራችን 09-67-44-22-04 እና 09-85-07-75-18 እንዲሁም በኮርፖሬሽናችን ዌብሳይት www.wwe.com.et እና https://www.facebook.com እንዲሁም ቴሌግራም https://t.me/Water Works Corporation Official መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን
