Tender Detail

Tender Details

  • Company በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 09 ጤና ጣቢያ
  • Address , Phone: 0114708252
  • Website
  • Deadline19 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price150.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-19 00:00:00
  • Categories Laboratory Equipment And Chemicals

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በግዥ መለያ ቁጥር 2/2018 ማለትም በሎት 1፡- ቋሚ ዕቃዎች፣ ሎት 2፡- የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች እና ሌሎችም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 09 ጤና ጣቢያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በግዥ መለያ ቁጥር 2/2018 ማለትም በሎት 1፡- ቋሚ ዕቃዎች፣ ሎት 2፡- የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች እና ሌሎችም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የጨረታ ማስከበሪያ ብር፡-

ሎት ቁጥር

 

የጨረታው አይነት

 

የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን

 

 

ሎት 1

 

ቋሚ ዕቃዎች

 

20,000.00

 

በተቋሙ ስፔሲፊኬሽንና በፎቶ

 

ሎት 2

 

የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች

 

40,000.00

 

 

 

በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት: -

1.     በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ወረዳ 09 ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 11 ቀርበው መገዛት ይችላሉ።

3.     የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው መሰብሰብያ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተባለው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

4.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት በጤና ጣቢያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 11 ለጨረታ በተዘጋጀ ውሳጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት የመ/ቤቱ ፍላጎት (ስፔሲፊኬሽን) ለሚያስፈልጋቸው ሎቶች በጥንቃቄ በስፔሲፊኬሽኑ መሰረት ብቻ መሞላት አለበት።

6.     ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

7.     የዘገየ ጨረታና በጨረታው መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

8.     አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9.     ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጤና ጣቢያ ሳሪስ ካዲስኮ ዝቅ ብሎ ቴሌ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 0114708252/0114406261

 

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 09 ጤና ጣቢያ

Save Tender