Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጉንችሬ ፡ ጉራጌ ዞን ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0910106716
  • Website
  • Deadline21 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-21 00:00:00
  • Categories Equipment And Accessories , Equipment

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ እና አዲስ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 001/06/2018

 

1.       በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ እና አዲስ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

•         ያገለገሉ የሞተር ሳይክል ፓርቶች

•         ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች

•         አዲስ የትራክተር እና የሳይክል ጎማዎች

•         ያገለገሉ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች

•         የተለያዩ ብረታ ብረቶች

•         ባለ 10000 ሊትር የብረት ታንከር

•         ያገለገሉ ጀነሬተሮች

•         የአንቡላንስ ቦዲና ሻንሲ

•         ያገለገሉ የውሀ ፓምፕ

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች:

1.       ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ከጠቅላላ ገንዘብ ሎት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/በጥሬ ብር/ በእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው፡፡

2.       ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው ዕቃዎች እኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት አጠቃለው በአንድ ጊዜ መውሰድ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡

3.       ተጫራቾች ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ በእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ፡፡

4.       ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው::

5.       ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስሪያ ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው::

6.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከ28/6/2018 ቀን ጀምሮ እስከ 12/7/2018 እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡

7.       ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም፡፡

8.       መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

9.       የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይዛወራል፡፡

ለበለጠ ረጃ በስ.ቁ. 0910106716/0928011746/ ይደውሉ ጉንቸሪ

 

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender