Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽህፈት ቤት የተለያዩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ"EU” በጀት ሎት (1) ፡ ለተሁለደሬ ወረዳ ግብርና ል/ጽ/ቤት የኤክስካቫተር ማሽንና ገልባጭ መኪና ኪራይ፣ ሎት (2) ጋቢዮንና የጋቢዮን ማሰሪያ ሽቦ፣ በመደበኛ በጀት ሎት (3) ለተሁለደሬወረዳ ውሃና ኢ/ል/ጽ/ቤት የመጠጥ ውሃ ግንባታ ዕቃዎችን፣ ሎት (4) የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት (5) የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ ሎት (6) ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን፣ ሎት (7) የእንስሳት መድሃኒት፣ ሎት (8) የእንስሳት ህክምና መሳሪያዎች፣ ሎት (9) የኤክስ ካቫተር ማሽን፣ ግሬደር፣ ሮሎ ኮምፓክተር፣ገልባጭ መኪና፣ የውሃ ቦቴና ሎቤድ ተሽከርካሪ ኪራይ፣ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮጀክት በጀት ሎት (10) የእንቁላል ጣይ ዶሮ መኖ በግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

1.     ህጋዊና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያለው፣

3.     የተጨማሪ እሴት(ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣

4.     ከላይ የተዘራዘሩት ማስረጃዎች ጎላ ብለው መነበብ መቻል አለባቸው፡፡

5.     ጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣

6.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት (1) እና (9) ለተቀመጡ ግዥዎች ብር 50000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ ሎት (2) ፣ (3) እና (5) ለተቀመጡ ግዥዎች ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) ፣ እንዲሁም ሎት (4) ፣ (6) ፣ (7) ፣ (8) እና (10) ለተቀመጡ ግዥዎች ለእንዳንዳቸው ብር 10000.00 (አስር ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣

7.     የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ከ27/06/2018 እስከ 12/07/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣

8.     ጨረታው በ12/07/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል (ባይገኙም ይከፈታል) ። የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን መክፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፣

9.     አሸናፊ የሚለየው በሎት (በድምር ዋጋ) ነው። በሰነዶቹ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል። አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች ጽ/ቤቱ በጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፣

10.  ከወቅቱ ገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፣

11.  ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ(በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

12.  ሁሉም የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፣አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎቹን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍሎቹ አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፣

13.  ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብና ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣

14.  ጨረታውን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፣

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 0012 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተለሁደሬ ወረዳ ገንዘ ጽ/ቤት

Save Tender