የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፎቶግራፍ መሳሪያዎች መበግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር AAM 08/2018
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፎቶግራፍ መሳሪያዎች መበግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 የፎቶግራፍ መሳሪያዎች ግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር ... 50,000
በዚሁ መሠረት ተጋባዥ ተጫራች ድርጅቶች :-
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀትና የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000050280873 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመጫረቻ ሰነዱ በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምከር ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 413 ለተከታታይ 8 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት (አርብ ዝግ ሆኖ ቅዳሜ ከፍት ነው) መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የቴክኒካልና ዶክመንት ኦርጅናል እና 1 ኮፒ እና ፋይናንሻል ዶከመንት ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የነጠላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ስሙ ጦር ሀይሎች በሚገኘው ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ምክር ቤቱ በሚያመቻቸው አዳራሽ 5፡00 ይከፈታል፡፡
5. የፎቶግራፍ መሳሪያዎቹ ዝርዝር መግለጫ በፅሁፍ እና በፎቶ የተደገፈ ካታሎማ ከቴክኒካል ዶክመንት ጋር አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
6. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ስም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይንም ለ60 ቀን የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
1. በጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ የድርጅቱ ኩብ ማህተምና ፊርማ ማድረግ እንዲሁም ዋጋ የሚሞላው በም/ቤቱ ዋጋ ማቅረቢያ ብቻ ሆኖ ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል።
2. ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት።
3. 8ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ (አርብን ጨምሮ) በቀጣዩ የመንግስት የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ጨረታው ይከፈታል፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት።
5. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
6. ምክር ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7. ጨረታው ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 09 22 73 16 27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
