Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ክልል የጌዲኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address ጌዲኦ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251-916-319153
  • Website
  • Deadline02 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-02 00:00:00
  • Categories Construction Works

በደቡብ ክልል የጌዲኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በተገኘ የበጀት ድጋፍ በገደብ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አማካኝነት የሚገነባ የቁም እንስሳት ገበያ ማዕከል ግንባታ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

በደቡብ ክልል የጌዲኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ገ/ወ/FSRP/01/2018

የግዥ መለያ ቁጥር ET-SER-FSR+B6:F49P-GEDEB-WOREDA-518963-CW-RFQ

 

በደቡብ ክልል የጌዲኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በተገኘ የበጀት ድጋፍ በገደብ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አማካኝነት የሚገነባ የቁም እንስሳት ገበያ ማዕከል ግንባታ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉት፡-

1.     ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣ የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት፤ በእቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

2.     ተጫራቾች በጽ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከ24/06/2018 ዓ/ም ጀምሮ ተከታታይ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከጽ/ቤቱ ገደብ ወረዳ ፋይፕ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስር ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፣

3.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በሲፒኦ በገደብ ወረዳ ፋ/ፕ/ጽ/ቤት ስም አሰርተው እስከ 24/07/2018 ዓ/ም ከሰዓት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ የዋጋና ቴከኒካል የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለባቸው። ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

4.     የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው ስለሚከፈት የጨረታ አከፋፈቱን ስነ-ስርዓት መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገደብ ወረዳ ፋዮ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በ24/07/2018 ዓ/ም 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

5.     የግንባታው የሳይት ቦታ በገደብ ወረዳ ባንቆ ጨልጨሌ ቀበሌ ይገኛል፡፡

6.     የግንባታው የማጠናቀቂያ ጊዜ የውል ስምምነት ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ በ120 ቀናት ውስጥ ይሆናል።

7.     የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ120 ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡

8.     ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡

9.     በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የግንባታ ስራው የመወዳደሪያ ሀሳብ ደጋፊ ሰነዶች በግልጽና በጥራት መግለጽ አለባቸው፡፡ ይህም የሚሆነው ከላይ በተገለጸው የግዥ መለያ ቁጥር መሰረት ሆኖ ከተገለጹት ጉዳዬችና ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመና ተቀባይነት ያላቸው መሆን አለባቸው።

10. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ሌሎችም ተጨማሪ ማረጋገጫዎች የሚመለከተው ሀላፊ ፊርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ሊሰረዝ ይችላል፡፡

11. ጽ/ቤታችን የዚህን ግንባታ ግዥ የሚፈጽመው የተዘረዘሩትን ሁኔታዎችና ቴክኒካል መመዘኛዎች ከሚያሟሉት መካከል በአለም ባንክ ግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች የግዥ ትዕዛዝ በመስጠት ይሆናል፡፡

12. አሸናፊ ተጫራች የውሉን 10 ፐርሰንት የውል አፈጻጸም ዋስትና በተጨማሪ የማህበራዊና የአካባቢ ደህንነት የውሉን 1% ፐርሰንት የአፈጻጸም ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

13. አሸናፊ ተጫራች የውሉን 20 ፐርሰንት የቅድመ ክፍያ ሲጠይቅ ተመጣጣኝ የባንክ ጋራንቲ ሲያቀርብ የሚከፈል ይሆናል፡፡

14. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. በጨረታው ላይ ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች በጽ/ቤቱ አድራሻ በኩል ምላሽ ማግኘት ይቻላል፡፡

16. የጽ/ቤቱ አድራሻ በገደብ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡

 

ስልክ ቁጥር፡- +251-916-319153+251-910-921610/251-926-060167

 

በደቡብ ክልል የጌዲኦ ዞን የገደብ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender