የመንቆረር ኮንስትራከሽን ድርጅት በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለክሬሽር ፕላንት ጠጠር ግብአት አቅርቦትና ፍንዳታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
Menkorer Construction Enterprize (የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንቆረር ኮንስትራከሽን ድርጅት በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለክሬሽር ፕላንት ጠጠር ግብአት አቅርቦትና ፍንዳታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1) ተጫራቾች የምትጫረቱትን ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ማስገባት አለባችሁ።
2) ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3:30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በበአላት ቀን ከሆነ በተጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ ጨረታን ከመከፈት አያግደውም።
3) ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፤ የዘመኑን ግብርየነበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
4) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመቅረብ 200.00 / ሁለት መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
5) ተጫራቾች የፋይናንሽያል ኦሪጅናል ሰነዶችን በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠ/ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
7) ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
8) አሸናፊው ድርጅት የሚሰራቸው የፈንጅ ፍንዳታ ስራ በተቀመጠለት ዝርዝር መሰረት በባለሙያ ተረጋግጦ ማለፍ አለባቸው።
9) አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
10) አሸናፊው ድርጅት ያሸነፉትን የፈንጅ አቅርቦትና ፍንዳታ ስራ በራሱ ትራንስፖርት ሙሉ ማቴሪያል አቅርቦ ደ/ማርቆስ ከተማ ድርጅቱ ክሬሽር ፕላንት በማቅረብ ማፈንዳት ይኖርበታል፡፡
11) ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለባቸው፡፡
12) ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0920514407 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት
