Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል 2018 ዓ.ም በጀት አመት ሁለተኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለማእከሉ አገልግሎት የሚውሉ የላብራቶሪ እቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች ኤሌክትሪክ እቃዎች እና ኮንስትራክሽን እቃዎች ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች እና ጸረ ተባይና ጸረ-ፈንገስ ኬሚካሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል 2018 ዓ.ም በጀት አመት ሁለተኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለማእከሉ አገልግሎት የሚውሉ የላብራቶሪ እቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች ኤሌክትሪክ እቃዎች እና ኮንስትራክሽን እቃዎች ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች እና ጸረ ተባይና ጸረ-ፈንገስ ኬሚካሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም፡-

1.     በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸው

3.     የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5.     ተጫራቾች ኦርጅናል ዕቃ መሙላት እና ያሸነፉባቸውን ዕቃ በባለሙያ ሊፈተሽ ይችላል።

6.     የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላል።

7.     ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ መክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ማግኘት ይቻላል።

9.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.P.O/ በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥፍ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሚያሰራ ተጫራች ከ60ቀናት ያላነሰ መሆን አለበት።

10. ከአንድ ሎት በላይ የሚወዳደር ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያው በእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ ለየብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል በድምር ማስያዝ አይቻልም፡፡

11. ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በማእከሉ የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት፡፡

12. አሸናፊው አካል የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.P.O/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዝ ይሆናል፡፡

13. ውድድሩ የሚካሄደው የላብራቶሪ እቃዎች በተናጠል ነው። ሌሎች እቃዎች ማለትም የጽህፈት መሳሪያዎች ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የውሃ እና ኮንስትራክሽን እቃዎች የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች እና ጸረ- ተባይና ጸረ-ፈንገስ ኬሚካሎች በጠቅላላ በሎት ድምር መሆኑን አውቃችሁ መሙላት ይጠበቅባችኋል፡፡

14. የላብራቶሪ እቃዎች የሚወዳደር ተጫራች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን በፎቶ የተደገፈ መረጃን ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

15. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

16. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ ቢሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 ሰአት ይከፈታል፡፡

17. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ማእከሉ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0980216262/0914051398/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

18. በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል

Save Tender