በአ/ብ/ክ/መ/በምስ/ጎጃ/አስ/ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ የደብረወርቅ የመጀ/ደ/ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የፋርማሲ ክፍል የአልሙኒየም /APTS/ ግንባታ የአገልግሎትና የእቃ አቅርቦት ግዥ እንዲፈጸምላቸው በጠየቁት መሰረት ግዥውን ለመግዛት ይፈልጋል።
የደብረወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአ/ብ/ክ/መ/በምስ/ጎጃ/አስ/ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ የደብረወርቅ የመጀ/ደ/ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የፋርማሲ ክፍል የአልሙኒየም /APTS/ ግንባታ የአገልግሎትና የእቃ አቅርቦት ግዥ እንዲፈጸምላቸው በጠየቁት መሰረት ግዥውን ለመግዛት ይፈልጋል፣ ስለዚህ፤
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
3. በግንባታ ዘርፍ GC ስራዎች ደረጃ 9 እና በላይ የሆኑ ተቋራጮች የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4. ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ለሚገመቱ የጨረታ ሰነዶች የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደ/ወርቅ የመጀ/ደ/ሆስፒታል ግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 50 ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ከጠቅላላ ዋጋ 1.5% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ገቢ አድርጐ የመሂ አንዱን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሲፒኦ ብሎ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን እና ፊርማቸውን በማስፈር በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሰነዱን ለማስገባት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 50 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ21 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ22ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ እለቱ የበዓላት ቀን ከሆነ፣ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት በመያዝ በአሸነፈበት የእቃውን /የአገልግሎቱን/ ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዥ ውል ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንከ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 50 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0586630611 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የደብረወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
