አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገሉ YTO-130 የሆነ የእርሻ ትራክተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሶስተኛ (3ኛ) ጊዜ የወጣ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ
አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገሉ YTO-130 የሆነ የእርሻ ትራክተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
1. ለጨረታው የወጡ የእርሻ ትራክተሮች የሆኑ ተሽከርካሪዎች 1ኛ የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 1238 መነሻ ዋጋ 1,985,000 (አንድ ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሺ ብር) 2ኛ የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 1239 1,750,530 (አንድ ሚሊየን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺ አምስት መቶ ሰላሳ ብር)
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአርባጉጉ የገ/ሕ/ስራ/ዩኒየን/ጽ/ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑንና ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ወይም መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ግለሰብ ወይም የገበሬ አበል የሆነ የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ አለበት፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታውን 10% በCPO በማቅረብ መጫረት ይችላሉ፡፡
5. ተሽከርካሪዎችን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ 10፡00 (ሰዓት) ድረስ በአርባጉጉ የገበሮች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ጊቢ ውስጥ ሙግር አካባቢ ታደሰ አበበ ህንፃ ጀርባ ማየት ይችላሉ።
6. ጨረታው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:30 (ሰዓት) ጀምሮ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የአርባጉጉ የገ/ህብረት ስራ ዩኒየን እዳማ መጋዘን ተዘግቶ በ5፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
7. ጨረታው በ16ኛ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 (ሰዓት) ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወሊሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት በ5፡00 (ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች የግል ድርጅት ወይም የመንግስት ድርጅት ከሆነ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡
9. ተጫራቾቹ ጨረታውን ካሽነፉበት ቀን ጀምሮ 10 ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ትራክተሮቹን መውሰድ አለባቸው፡፡
10. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
11. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በዩኒየኑ ጽ/ቤት በመገኘት ወይም
በስ.ቁ:- 0921096880/0920063165/0917034343 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
አድራሻችን፡- አርባጉጉ የገ/ሕ/ሥራ/ዩኒየን አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ አርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ሕ/ሥ/ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ
አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ
