Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደብረ ዘይት መንገድ መውጫ ፍተሻ ሳይደርስ የሺ ቶታል አለፍ ብሎ ወደ ግራ በሚወስደው መንገድ 800 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-4173226
  • Website
  • Deadline10 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-10 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair , Mechanical Work and Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማሽን ተከላ እና የማሽን እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ተ/ቁ

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

ሎት 1

የማሽን ተከላ

50,000.00

ሎት 2

የማሽን እና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና

50,000.00

 

ለ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ለኮሌጁ ለሥልጠና አገልግሎት የሚያገለግሉ ማሽኖች እና ኤሌክትሮኒክስ ለማስጠገን እና ለማስተከል እንዲሁም ማሽኑን አስነስቶ ሥልጠና ለመስጠት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት አለባቸው፡፡

1.     በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው።

2.     ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3.     በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከመንግሥት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ተጫራቾች በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ CPOውን ቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ በመከተት በደንብ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ኤንቨሎፑ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ተበሎ መገለፅ ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6.     ተጫራቾች ለተጫረቱበት ማሽን ተከላ እና የማሽን እና ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራ ተወዳዳሪው ባለበት ቦታ በማየት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡

7.     ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በ4:30 ጨረታው ይከፈታል፡፡

 

ማሳሰቢያ፡-

በጨረታው ተሣታፊ የሚሆነው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች ብቻ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- 011-4173226/011-8-495158/011-4-343336/

01114173226/

የመ/ቤቱ አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደብረ ዘይት መንገድ መውጫ ፍተሻ ሳይደርስ የሺ ቶታል አለፍ ብሎ ወደ ግራ በሚወስደው መንገድ 800 ሜትር ገባ ብሎ ነው።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Save Tender