Tender Detail

Tender Details

  • Company ደብረብርሃን/ክ/ሙ/ብ/ም/ማ/ማ/ግ/ፋ/ን/አሰ/ቡድን
  • Address ደብረብርሃን ከተማ ሼል ኦሬንታል ካፌ ፊት ለፊት አቶ ብሩክ ነጋሽ ሕንፃ ላይ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 637 66 58 /59
  • Website
  • Deadline09 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-09 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair , Stationery Materials , Electronics Materials

የደብረብርሃን ክላስተር የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከል ግዥ ማዕከል ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መግዛት ይፈልጋል።

ደብረብርሃን/ክ/ሙ/ብ/ም/ማ/ማ/ግ/ፋ/ን/አሰ/ቡድን


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደብረብርሃን ክላስተር የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከል ግዥ ማዕከል ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውል

•        ሎት 1፡- የፅሕፈት መሣሪያ (እስቴሽነሪ)፣

•        ሎት 2፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

•        ሎት 3፡- ኤሌክትሮኒክስ ጥገና በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

በዚህ መሰረት፡-

1)     በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2)     በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና የቲን /TIN/ እና ቫት ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ተያያዥ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3)     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደብረብርሃን ክላስተር ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ16/06/2018 ዓ/ም ጀምሮ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ።

4)     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ለሎት፡- 1 የፅሕፈት መሣሪያ (እስቴሽነሪ) 2,000 (ሁለት ሺ)፣ ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 7,000 (ሰባት ሺ)፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና 1,000 (አንድ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረብርሃን ክላሰተር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5)     ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ ወይም አንድወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብርሃን ክላስተር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 እስከ 15ኛው ቀን ማለትም በ 30/6/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6)     ጨረታው በ15ኛው ቀን ማለትም በ30/06/2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 11፡30 ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4፡00 ቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል። ሆኖም የጨረታ መክፈቻው እለት የሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

7)     ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የመወዳደሪያ ሃሳብ በሌላኛው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የለበትም።

8)     አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት)ተከታታይ ቀናት ውስጥ በደብረብርሃን ክላስተር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በመገኘት ውል መፈረም ይኖርበታል።

9)     ውል የማይፈፅሙ አሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዘውን ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ በማድረግ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።

10)                        የጨረታ ግምገማው በጥቅል ወይም በተናጠል ድምር የሚካሄድ በመሆኑ ተጫራቾች የሁሉንም እቃዎች በተቻለ መጠን ዋጋ ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የሚቀርቡት እቃ በተቀመጠው ሳምፕል እና በተያያዘው እስፔስፊኬሽን ብቻ ይሆናል።

11)                        በጨረታው ለመሳተፍ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም በአካል ቢሮ ቁጥር 07 ወይም 011 637 6658/59 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

12)                        መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ማሳሰቢያ፡- አድራሻ ሼል ኦሬንታል ካፌ ፊት ለፊት አቶ ብሩክ ነጋሽ ሕንፃ ላይ።

 

ደብረብርሃን/ክ/ሙ/ብ/ም/ማ/ማ/ግ/ፋ/ን/አሰ/ቡድን

ደብረብርሃን

Save Tender