በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓ.ም ለከተማ አስተዳደሩ ቢሮ ግንባታ የሚሆኑ የግንባታ ማቴሪያል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓ.ም ለከተማ አስተዳደሩ ቢሮ ግንባታ የሚሆኑ የግንባታ ማቴሪያል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ
3. የግብር ከፍያ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፣
4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው
5. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት ሺህ ብር/ እና ከዚያም በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገበ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ 14,000 /አስራ አራት ሺህ ብር/ ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 /ሶስት ሰዓት ተኩል/ ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል።
ጨረታው በዚሁ ቀን 3፡31/ሶስት ከሰላሳ አንድ/ ተዘግቶ 4፡00 /አራት ሰዓት/ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ውስጥ ይከፈታል።
8. የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፌኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላል። የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 የሰነድ ክፍያ በመፈጸም የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመያዝ ከግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
10. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑ ይታወቃል።
11. ጨረታው ተሳታፊዎችን ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙሊያው ላይ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ማህተም የሌላቸው ተጫራቾች ህጋዊ ፊርማችሁን ማስቀመጥ ይኖርባችኋል።
12. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው።
13. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ባዘጋጀው ሳይት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
