በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት በወረዳው ለሴክተር መ/ቤቶች የቢሮ አግልግሎት የሚውል B+G+7+T U'ንፃ ግንባታ ደረጃ 2 Gc/1Bc እና በላይ የሆኑ ህጋዊ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
ግዢ መለያ ቁጥር 04/2018
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት በወረዳው ለሴክተር መ/ቤቶች የቢሮ አግልግሎት የሚውል B+G+7+T ህንፃ ግንባታ ደረጃ 2 Gc/1Bc እና በላይ የሆኑ ህጋዊ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ /Tax Clearance/ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ቁጥር፣ የንግድ ምዝገባ ማስረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው፣
3. በፋይናንስ ቢሮ የአቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገቡ ወይም E-GP የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፤
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከታወቀ የፋይናንስ ተቋም 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ወይም መሂ1 ኮፒ ተቆርጦ በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
5. ተጫራቾች ለግንባታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለት 20 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 1000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ በመክፈል በእንሳሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ የድርጅቱ ባለቤት የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ "የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ/ Tax Clearance / ኦርጂናል ሰነዶችን ይዞ መምጣት መውሰድ የሚችሉ ይሆናል፤
6. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ሰነድ ሁለት ኮፒ ማለትም ሁለት ኮፒ የፋይናንሽያል ሰነድ፣ ሁለት ኮፒ የቴክኒካል ሰነድ ለየብቻው በአንድ እናት ፖስታ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን በመ/ቤታችን ግዢ ቢሮ ቁ.3 4:00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ሰዓት ከአብከመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮና የዞን መምሪያዎች ወይም ንግድ ፈቃድ ካወጡበት አካባቢ ካሉ የከተማ ልማት ቢሮና መምሪያዎች በእጃቸው ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ከ70 ፐርሰንት በላይ ያጠናቀቁ ስለመሆናቸው የጽሁፍ ማስረጃ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፤
9. ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግንባታው 22 ቀን ለማሸግ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
10. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ መ/ቤቱ በሚያዘጋጀው ፎርም ላይ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው፤
11. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁ.3 በአካል በመምጣት እንዲሁም በስልክ ቁ.0111190270/280 እንዲሁም በቴሌግራም ቻናል t.me/Ensarowereda መከታተል ይችላሉ፡፡
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
