በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መንግሥት በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት የውሃ ፓምፕ ሞተርና ፓናል ቦርድ በዘርፉ ሕጋዊ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መንግሥት በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት የውሃ ፓምፕ ሞተርና ፓናል ቦርድ በዘርፉ ሕጋዊ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2018 ያሳደሱ እና የ2017 ዓ.ም ግብር ያጠናቀቁ፡፡
2. የቲን ነምበርና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚዛን አማን ከተማ አስተደደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት በመቅረብ በብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በግልጽ በመሙላት ስምና ፊርማ በማኖር ኦርጅናልና 2 ኮፒ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀኖች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በሚዛን አማን ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. አሸናፊው ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ እስከ 7 ቀን ውስጥ ያሸነፈበትን በዝርዝሩ መሠረት ለድርጅቱ ማስረከብ አለበት፡፡
7. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚያውኑ ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
• መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
• ተጫራቾች ከአሁን በፊት የሰሩትን የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
• ለበለጠ መረጃ- በስልክ ቁጥር 09-17-79-74-12 ወይም 09-17-15-11-28 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
