Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0465511292
  • Website
  • Deadline07 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-07 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የተለያዩ ያገለገሉ ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢመአ ሶዶ ዲስትሪክት 06/2018 ዓ.ም

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የተለያዩ ያገለገሉ ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በመንግስት የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ብቁ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1.       ተጫራቾች በድርጅት ሥም ወይም በግለሰብ ደረጃም መጫረት የሚቻል ሲሆን በድርጅትም ይሁን በግለሰብ ደረጃ ቲን ነምበር ያለው መሆን አለበት።

2.       ተጫራች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በመ/ቤታችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000322276919 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ ባለው ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ መውሰድ ይችላሉ።

3.       ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ከሰኞ-ዓርብ የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

4.       ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡20 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5.       ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 046-551-1292 መደወል ይችላሉ።

6.       የንብረቶቹ ዝርዝር መነሻ ዋጋ የተቀመጠ ቢሆንም አሸናፊ መሆን የሚችለው በጥቅል በቀረበው ዋጋ ነው።

7.       ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት በኋላ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ገንዘቡን ከላይ በተገለፀው ሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ አለበት።

8.       አሸናፊው ገንዘቡን ገቢ ካደረገ በኋላ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ንብረቱን ሙሉ በሙሉ መረከብ አለበት።

9.       መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-046 551 1292/ፖ.ሳ ቁጥር 116

አድራሻ ወላይታ ሶዶ ከነዳጅ ዲፖ አለፍ ብሎ ጎፋ ማዞሪያ

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ መንገድ ጥገና ዲስትራክት

 

Save Tender