በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸዉ ግንባታዎች የግንባታ ቁጥጥር፣የኮንትራት አስተዳደር እና የዲዛይን ማሻሻያ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ አማካሪዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን እንዲጠናቀቅ የሚያስችል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በ
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት
የግንባታ አማካሪ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር .የካ/ዲ/ግ/ስ/ጽ/ቤት002/2018ዓ.ም
በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸዉ ግንባታዎች የግንባታ ቁጥጥር፣የኮንትራት አስተዳደር እና የዲዛይን ማሻሻያ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ አማካሪዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን እንዲጠናቀቅ የሚያስችል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ሎት ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡
|
ሎት |
የስራው ዓይነት |
ግንባታ ጊዜ (በቀን) |
ደረጃ |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን |
የጨረታ ሰነድ የሚገባበት ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
1 |
ወረዳ 10 ሚሊኒየም ት/ቤት አጥር ግንባታ |
30 |
ጥቃቅን ልዩ 1 |
ከተደራጁበት የዋስትና ደብዳቤ |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት |
|
2 |
ወረዳ 02 የደረቅ ቆሻሻ ቅብብሎሽ ጣቢያ ግንባታ |
45 |
ጥቃቅን ልዩ 1 |
ከተደራጁበት የዋስትና ደብዳቤ |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት |
|
3 |
ወረዳ 10 የደረቅ ቆሻሻ ቅብብሎሽ ጣቢያ |
45 |
ጥቃቅን ልዩ 1 |
ከተደራጁበት የዋስትና ደብዳቤ |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት |
|
4 |
ወረዳ 06 ጂ+0 የህጻናት የቀን መቆያ ግንባታ |
30 |
ጥቃቅን ልዩ 1 |
ከተደራጁበት የዋስትና ደብዳቤ |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት |
|
5 |
ወረዳ 12 ጂ+0 የህጻናት የቀን መቆያ ግንባታ |
30 |
ጥቃቅን ልዩ 1 |
ከተደራጁበት የዋስትና ደብዳቤ |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት |
|
6 |
የየካ ክፍለ ከተማ የመኪና ማቆሚያ ጥላ (shade) |
30 |
ጥቃቅን ልዩ 1 |
ከተደራጁበት የዋስትና ደብዳቤ |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት |
|
7 |
የተቀናጀ የከተማ ግብርና( የዶሮ አሳ፤ኮምፕሌከስ ግሪን ሀዉስ (ሀይድሮፎኒከ)፡እና ንብ እርባታ) |
60 |
ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ |
50,000.00ብር |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት |
ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት |
1. ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የ2018 ዓ.ም የሚያገለግል ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በ2018ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ከሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው -(supplier list) ፣ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡ በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስራ ላላቸዉ ስራ አማካሪዎች ደግሞ ያላቸዉ የግንባታ አፈፃፀም ከ 75 ፐርሰንት በላይ መሆኑን የሚገልፅ መልካም አፈፃፀም (Good Performance) ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሃያ አንድ ተከታታይ ቀናት ዘወትርበስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በ4ኛ ፎቅ ላይ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Origi-nal) እና የማይመለስ ቅጂ(copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ በጨረታው የቴክኒካል ሰነድ ከከፍል ውስጥ ባለው መሰረት ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት በየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ለየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት አሰርተው ማምጣት አለባቸው፡፡
5. ተጫራቶች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድን በጨረታው ሰነድ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት የመጫረቻ ሰነድ በማዘጋጀት፡-
6. ከሎት 1-06 ፋይናንሺያል ብቻ ስለሆነ ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል እና ፋይናንሽያል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ሶስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና ፖስታና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት በየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት (ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል)፡፡
7. ሎት7 ውድድሩ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል እና ቴከንካል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል እና ፋይናንሽያል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በማሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል ፡፡በተጨማሪም የታሸገውን 6 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና ቴክኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን ፖስታና የCPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት በየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደርዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት (ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል)፡፡የጨረታ መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁደ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይሰዐትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾች መመሪያን እንዲያነቡ እና የግንባታ ሳይቱን ማየት ይመከራል፡፡
9. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ባለሙያዎች በድርጅታቸው ውስጥ ብቻ የሚሰሩ ወይም ለድርጂቱ ብቻ የፈረሙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በድርጅቱ ኃላፊ ወይም ተመሳሳይተግባር እና ስልጣን በተሰጠው አካል እና በተቀጣሪው (በፈራሚው) ባለሙያ የተፈረ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ አንድ ባለሙያ ከአንድ አማካሪ ድርጅት በላይፈርሞ ከተገኘ ያስፈረሙት አማካሪዎች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡
10. የትኛውንም ከላይ የተዘረዘሩትን ሆነ በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማከበር፣ በሚያስገቡት የመጫረቻ ሰነዶች በሁሉም ገፆች ላይማህተም እና ፊርማ አለማድረግ ፣በዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና በዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
11. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የድርጅቱ የስራ ልምድ እና ማንኛውም በቴከኒካል የተጠየቁ ዶክመንቶችን አሰሪ መስሪያ ቤት ኦሪጅናል ዶከመንት የመጠየቅ እና ዶከመንቶቹን ከሰጠው አካል የማጣራት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. አድራሻ:- መገናኛ ማራቶን ህንጻ ፊት ለፊት የሚገኘው የከፍለ ከተማው ህንፃ የካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት አራተኛ ወለል በስተግራ በኩል፡፡
13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የየካ ክፍለ አስተደደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
