Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline09 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-09 00:00:00
  • Categories Cloth And Shoes

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የሀገር ባህል ቀሚሶችን ከአምራች ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር -SSNT-T603

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የሀገር ባህል ቀሚሶችን ከአምራች ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የሀገር ባህል ልብስ አምራች ድርጅቶች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል በዘርፉ ለመስራት የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አስፈላጊውን የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በተመሳሳይ አቅርቦት ዘርፍ ቢያንስ ሁለት (2) ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር/አንድ መቶ ብር/በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T603 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መቶ ስልሳ ሺህ ብር (160,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንከ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

4. ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል እስከ የካቲት 30 2018 ዓ.ም ጠዋት 10፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ጠዋት በ 5:00 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-8025

ኢ-ሜይል፡ WoldeM@ethiopianairlines.com

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Save Tender