የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሾኔ ምድብ ችሎት የዙሪያ አጥር ለማስገንባት የሥራ ተቋራጮችን ማህበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሾኔ ምድብ ችሎት የዙሪያ አጥር ለማስገንባት የሥራ ተቋራጮችን ማህበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ደረጃቸው BC-9/GC-9 (የኮንስትክሽን ማህበራት) የሆኑ እና ከዚያ በላይ የሆነ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈታድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይ/ን አስተዳደር ቢሮ ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካይ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በማስያዝ መግዛት ይችላል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስም ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክየተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርቦ ሥራውን የሚሰሩበትን የፋይናንሻል ኘሮፖዛል አንድ ኦርጂናል፤ ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶ/ሲ.ፒ.ኦ) ለየብቻ በስም በታሸገ ፖስታ በማድረግ (የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት) አምስቱን ፖስታዎች በሌላ አንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በሰም አሽጐና የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተበሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የአገልግሎት ዋጋው በሰነድ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሀዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው በ22ኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተቋሙ ግዥ ፋይ/ን አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ አሰሪው መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
• የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የግዢ መመሪያ 36/2018 ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
• ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ገበያ ዋጋ በታች ያቀረበ እንደሆነ አሰሪው መ/ቤት ውል ለመግባት አይገደድም፡፡
• አሰሪው መ/ቤት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር ከአጠቃላይ የስራ መጠን 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ውል መግባት ይችላል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0465552328/0465552339 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ሆሳዕና፤
