Tender Detail

Tender Details

  • Company የሶዶ ቀጣና እንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶሪ ማዕከል
  • Address ወላይታ ሶዶ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 5512593
  • Website
  • Deadline09 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-09 00:00:00
  • Categories Laboratory Equipment And Chemicals , Construction Machinery

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ቀጣና እንስሳት ጤና ጥበቃ ላቦራቶር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የሶዶ ቀጣና እንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶሪ ማዕከል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ቀጣና እንስሳት ጤና ጥበቃ ላቦራቶር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም፡

•        ሎት 1 የላቦራቶሪ ኬሚካሎችን

•        ሎት 2 ፕላንት ማሽነሪ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ እየጋበዝን፤

1.       የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር አጠናቃችሁ የከፈላችሁ በመንግሥት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገቡ የቫትና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፤

2.       የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፤

3.       የጨረታ አሸናፊ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፤

4.       ተጫራቾች የሰጡትን የአንዱን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻ በመግለጽ በወላይታ ሶዶ ቀጣና እንስሳት ጤና ጥበቃ ላቦራቶር ሂሣብ ክፍል በተዘጋጁ የጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።

5.       ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀን ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

6.       ጨረታ የሚከፈተው ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7.       መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

 

ማሳሰቢያ፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: 046 5512593 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

የሶዶ ቀጣና እንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶሪ ማዕከል

Save Tender