በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተገለፀውን በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ ለኃይል አገልግሎት የሚያስፈልገውን Solar 150KVA በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተገለፀውን በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ ለኃይል አገልግሎት የሚያስፈልገውን
1. Solar 150KVA በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅደም ተከተል ሁኔታዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።
2. የዘመኑን ማለትም የበጀት ዓመቱን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው።
4. ጨረታውን አሸንፎ የሚያቀርበውን ዕቃ/ ንብረት ጥራቱን ለማረጋገጥ ናሙና ማቅረብ የሚችል።
5. ጨረታውን ያሸነፉ ግለሰብ አቅራቢ ድርጅት ዕቃውን/ ንብረቱን እስከ ሆስፒታሉ በእራሱ ወጪ የሚያቀርብ።
6. አሸናፊ ሆኖ የሚጠራው ግለሰብ አቅራቢ ድርጅት የዕቃውን የንብረቱን ጥራትና ደረጃ በጨረታ ሰነድ ላይ ሆስፒታሉ ባስቀመጠው መልኩ ውል ገብቶ በውሉ መሠረት የሚያቀርብ።
7. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ለተከታታይ ዘወትር የሥራ ሰዓት እና ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/ አ/ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ወይም በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታውን እንዲያስገቡና በተገለፀው ቀን የሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አ/ደጋፊ ሥራ ሂደት ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዘርፍ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በመሥሪያ ቤቱ ስም ለቦና ሆስፒታል ማስያዝ ይኖርበታል።
10. ጨረታው የሚገባበት ቀን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የሥራ ቀናት ተቆጥሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሕጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን ያላሟላ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታውን የሚገባበት መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀንና ሰዓት ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0926 38 48 50 / 09 68 61 55 23 / 09 16 37 27 54 / 09 16 40 15 99 ደውሎ መረዳት ይችላል።
በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ጤና ቢሮ ስር የቦና አጠቃላይ ሆስፒታል
