Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት በከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ , Phone: 0476680200
  • Website
  • Deadline13 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-13 00:00:00
  • Categories Construction and Water Works , Water Construction

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/ መንግስት በከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ካሉት ቀበሌዎች ከዚህ በታች በሎት በተቀመጡ ቀበሌዎች የምንጭ ውሃ የግንባታ ሥራ በተቋሙ ባለው መደበኛ በጀት ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት በከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018

 

በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/ መንግስት በከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ካሉት ቀበሌዎች ከዚህ በታች በሎት በተቀመጡ ቀበሌዎች የምንጭ ውሃ የግንባታ ሥራ በተቋሙ ባለው መደበኛ በጀት ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ሀ. በሎት 01/ቢጋ፣ እራሞ፣ ወዳፋ፣ እሸታ፣ ጮመቻ እና ኦላ /ቀበሌ/ 6 ምንጭ ውሃ ግንባታ/፣

ለ. በሎት 02/ጊዳ፣ ኡፋ ገነት፣ ጎፓ፣ ኦማ ሾንጋ እና ቡባ /ቀበሌ/5 ምንጭ ውሃ ግንባታ/፣ በአጠቃላይ ከላይ ከተራ ቁጥር ሀ-ለ በተቀመጡ ቀበሌዎች የውሃ ምንጭ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ከደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የሆነ (የጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ /GC/ ወይም የውሃ ግንባታ /Gwc/ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸውን ድርጅቶች ወይም ማኅበራት አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባችኋል

1.     በዘመኑ የታደሰ ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ ያለው፣

2.     በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣

3.     የቫት/ቲኦቲ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

4.     ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል /ለማኅበራት ብቻ/፣

5.     የአቅራቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችል፣

6.     የንግድ ምዝገባ እና ቲን ነምበር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

7.     አንድ ግንባታ ድርጅት መወዳደር የሚችለው በአንድ ሎት ብቻ ነው፣

8.     መልካም የሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ከህጋዊ ተቋም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

9.     በወረዳው ውስጥ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ አሸንፎ ሥራውን በማስተጓጎልም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸውን ድርጅቶች ወይም ማኅበራትን ጨረታው አያሳትፍም፣

10. ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነድ ሁለት ሁለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ለሎት 01 ብር የ40,000 /አርባ ሺህ ብር/፣ ለሎት 02 የ35,000 /ሰላሳ አምስት ሺህ ብር/ CPO በሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሠርተው ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በአማራጭነት ከተፈለገ በካሽ አድርገው በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ባለው የንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000261080808 ላይ ገቢ በማድረግ የባንኩን ስሊፕ ማስያዝ ይችላሉ፡፡

12. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ እየከፈሉ ከሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 5ት ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፣

13. ጨረታው በ22ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ታሸጎ በታሸገበት ዕለት ከሰዓቱ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

14. ተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሰነድ የመክፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡

15. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡

 

ማሳሰቢያ፡-

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 668 0200 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender