የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል፡- በድጋሚ የወጣ 147A የፕሪንተር ቀለም ፣ Grade Six and Grade Eight Correction and Management System (ሶፍትዌር ግዥ) እና Old Roster Management and file Handling System (ሶፍትዌር ግዥ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጨ 19/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል፡-
በድጋሚ የወጣ 147A የፕሪንተር ቀለም ፣ Grade Six and Grade Eight Correction and Management System (ሶፍትዌር ግዥ) እና Old Roster Management and file Handling System (ሶፍትዌር ግዥ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች:-
1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ያላቸው፡፡
3. የግዥው መጠን ብር ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል። ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/በመከፈል ከገንዘብ ያዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 13/15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ በድጋሚ የወጣ 147A የፕሪንተር ቀለም 50,000 /ሃምሳ ሺህ NC/ Grade Six_and Grade Eight Correction and Management System(ሶፍትዌር ግዥ) ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ / Old Roster Management and File Handling System (ሶፍትዌር ግዥ) ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል።
9. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብከመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል።
10. የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤
11. 147A የፕሪንተር ቀለም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
12. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብከመ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከፍል በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 62 67 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
13. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
