በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት የዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት በዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም ምዕራፍ ሁለት (OWNP-CWA-Phase-II) በ2018 በጀት ዓመት በዲመካ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት የታቀዱ የትምህርት ቤት ዋሸ ፋሲሊቲዎች ሎት 1. በዲመካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት ቤት ውስጥ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ክፍል ግንባታ (MHM) እና የቆሻሻ ማቃጠያ ግንባታ
በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት የዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት የዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት በዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም ምዕራፍ ሁለት (OWNP-CWA-Phase-II) በ2018 በጀት ዓመት በዲመካ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት የታቀዱ የትምህርት ቤት ዋሸ ፋሲሊቲዎች ሎት 1. በዲመካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት ቤት ውስጥ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ክፍል ግንባታ (MHM) እና የቆሻሻ ማቃጠያ ግንባታ (Incinerator) ሎት 2. በዲመካ ከተማ አስተዳደር በሽዳ ቀበሌ ጤና ኬላ መፀዳጃ ቤት (latrine) የቆሻሻ ማቃጠያ (Incinerator) ግንባታ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን የግንባታ ሥራዎችን ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማደራጀት ኃላፊነት በተሰጣቸው አካላት የተደራጁ ብቻ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. ደረጃ ዘጠኝ እና በአዲሱ ደረጃ ስምንት እና ከዚያ በላይ በግንባታ ሥራ ዘርፍ የተደራጁ ማህበራት መሆን አለባቸው፡-
2. ለ2018 የበጀት ዓመት ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተጠቀሰው ደረጃ መሠረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው:-
3. ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
4. የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፡-
5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፡-
6. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
7. የግብር ግዴታን በመወጣት ስልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን ለበጀት ዓመቱ /2018 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታደሰ የታከስ ከሊራንስ ሠርተፍኬት የያዘ/Valid tax clearance for 2018 EFY budget year/:-
8. ከዚህ ቀደም በወሰዳቸው ውሎች በጥራትና በወቅቱ የሚያሥረከብ፣ የጥራት ማጓደል፣ ማዘግየት፣ ውል ማቋረጥ…ወዘተ የውል አስተዳደር አፈፃፀም ችግር የሌለበት ከዚህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀከት ወስዶ በግንባታ ወይም በፕሮጀከት የውል ስፔስፍከሽን እና ማጠናቀቂያ ቀናት በሚፈለገው ጥራትና የማጠናቀቂያ ቀናት በማጠናቀቅ ለአሰሪው ባለበጀት መ/ቤት በወቅቱ ያስረከበ ውል ያላቋረጠ ተጫራች ብቻ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
9. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርቦ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ከፍለው በመግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ በዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት ስም ከታወቀ ወይም ስልጣን ከተሰጠው ባንክ ወይም ተቋም በእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 በሲ.ፒ.ኦ ብቻ በማዘጋጀት ከጨረታው ዶክመንት ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
11. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አርጅሉ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒው ላይ ኮፒ በማለት በማሸግ ለዚህ ጨረታ ሥራ በተዘጋጀ በዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል ጨረታው በሃያ ሁለተኛው /22ኛው/ቀን የሥራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በዚህ ዕለት 6፡30 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
12. የተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪሎቻቸው በወቅቱ ያለመገኘት የጨረታውን ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
ማሳሰቢያ፡-
መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913000124 በመደወል መረዳት ይቻላል፡፡
በዲመካ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስና ፕላን ዩኒት
