የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል ያገለገለ መኪና በሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መወዳደር ይቻላል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት አርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል ያገለገለ መኪና በሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መወዳደር ይቻላል።
1. ተጫራቾች ዝርዝር የመጫረቻ ሰነድ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ለ15 ተከታታይ ቀናት ብር 1000(አንድ ሺ ብር) በመክፈል ከአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አሰ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ)ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው የሚከናወነው ህጋዊ ተጫራቾች በተገኙበት በማዕከሉ ግቢ ይከናወናል ።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል ቅጥር ግቢ ይከናወናል።
5. የጨረታ መክፈቻ በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
6. ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት ወይም ለመግዛት የፈለገውን ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ካላስያዘ መወዳደር አይችልም::
7. ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዘው ገንዘብ ለተሸናፊው የጨረታው ሂደት እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
8. ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃዎች ካሸነፈበት ቀን 5/አምስት ቀናት /ውስጥ ሙሉ ክፍያ ፈጽሞ ማንሳት ግዴታ አለበት።
9. ከላይ በተራ ቁጥር 8 በተገለጸው መሠረት በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሙሉ ክፍያ አጠናቀው ያሸነፈውን እቃ ባያነሱ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ይሆናል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ክፍል ወይም በስልክ ቁጥር 0468841883 /0468810322/0468811598 ወይም 0913034259/0912765085/ 0913820570 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
የአርባምንጭ አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከል
