በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሞተር ብስክሌት እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሞተር ብስክሌት እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተለውን የመወዳደሪያ መስፈርት በማሟላት መወዳደር ይኖርባቸዋል፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
2. ግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ከፍያ ንብረት አስ/ር ደጋፍ የሥራ ሂደት እየመጡ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፣
5. በባንክ የተረጋገጠ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ የያዘ C.P.O ከሠነዱ ጋር ማቅረብ ይቅርባቸዋል፣ ለጨረታው መወዳደሪያ የሚቀርብ C.PO በባንከ ማህተምና በባንክ ኃላፊ ሠራተኞች ፊርማ የተረጋገጠ መሆን አለበት፣
6. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶቻቸውን ኦርጅናሉንና የኦርጅናል ኮፒ በፖስታ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ መጨረሻው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዶቻቸውን ማስገባት አለባቸው። የዕቃውን ጥራት በጥንቃቄ እናያለን፣
7. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት ቀናት/ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በሣጥኑ መጨመር አለባቸው። በዕለቱ 5፡30 ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ማለትም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሕጋዊ ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ለጨረታው በዝርዝር ከተጠየቀው ዕቃ ዓይነት ውጪ ለመወዳደር ማቅረብ አይቻልም፣
9. በጨረታው ሠነድ የተፃፈውን የዕቃ ዓይነት ተጫራቾች በትክክል መሙላት አለባቸው፣ የሚያቀርቧቸው ዋጋ ከቫት ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
10. ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፣
11. ፍርድ ቤቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መለወጥ ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ አድራሻ በስልክ ቁጥር 0465512100 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
