Tender Detail

Tender Details

  • Company ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር
  • Address (የካ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 06፣ ዓድዋ ድልድይ ኮንዶሚኒየም) ከሴቶች አደባባይ ወደ ዓድዋ ድልድይ በቀኝ በኩል በግምት 300 ሜትር ላይ በሚያስገባው ኮብልስቶን ገባ ብሎ፡ ናቲ ጋራዥ በሚለው ታፔላ ኮንዶሚኒየም አጥር መጨረሻ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911660977
  • Website
  • Deadline20 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-23 00:00:00
  • Categories Vehicle

የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር ሲገለገልባቸው የነበሩትን 2 (ሁለት) ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ማለትም 1 (አንድ) ያገለገለ ቶዮታ ላንድክሩሰር እና 1 (አንድ) ኒሳን ፓትሮል ተሽከርካሪ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር


ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር ሲገለገልባቸው የነበሩትን 2 (ሁለት) ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ማለትም 1 (አንድ) ያገለገለ ቶዮታ ላንድክሩሰር እና 1 (አንድ) ኒሳን ፓትሮል ተሽከርካሪ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1.     ማንኛውም ተጫራች ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ከሴቶች አደባባይ ወደ ዓድዋ ድልድይ በቀኝ በኩል ኮንደሚኒየም ቤቶች ጀርባ በድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ጊቢ ውስጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ባሉት የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት የሚቻል ሲሆን ከሶስተኛው ቀን እስከ 9ኛው ቀን ኮፍን እየከፈቱ ውስጡን ማየት ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ከጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡

3.     የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡

4.     ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ያገለገለ አሮጌ መኪና የማጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ/ በአዲስ አበባ ከተማ (የካ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 06፣ ዓድዋ ድልድይ ኮንዶሚኒየም) ከሴቶች አደባባይ ወደ ዓድዋ ድልድይ በቀኝ በኩል ኮንደሚኒየም ቤቶች ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት፣ አስተዳደር ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም ይኖርበታል፡፡

5.     ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር የሥራ ቀናት/10 ቀናት ያገለገሉ መኪናዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው።

6.     አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በሶስት /3/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በአስር /10/ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ እና የማንሳት ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪው በድጋሚ ለጨረታ ሊቀርብ ይችላል፡፡

7.     ተጫራቾች ከድርጅቱ ግዥ ክፍል የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለተሽከርካሪዎቹ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር 10/ የሥራ ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ አስተዳደር ቢሮ ምድር ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡

8.     የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከፊት በሚመጣው ሰኞ ማለትም የካቲት 16 ቀን 4፡30 ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብት በአዲስ አበባ ከተማ (የካ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 06፣ ዓድዋ ድልድይ ኮንዶሚኒየም) ከሴቶች አደባባይ ወደ ዓድዋ ድልድይ በቀኝ በኩል በግምት 300 ሜትር ላይ በሚያስገባው ኮብልስቶን ገባ ብሎ፡ ናቲ ጋራዥ በሚለው ታፔላ ኮንዶሚኒየም አጥር መጨረሻ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

9.     ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ላይ የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በ0911660977 ደውለው መረጃ ማገኘት ይችላሉ ፡፡

 

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር

Save Tender