Tender Detail

Tender Details

  • Company በቤንች ሸኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት
  • Address ቤንች ሸኮ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0917988437
  • Website
  • Deadline03 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-03 00:00:00
  • Categories Construction Works

በቤንች ሸኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት ባለቤትነት በ2018 የበጀት ዘመን ሊያሰራ ላሰበው የቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ማሰራት ይፈልጋል።

በቤንች ሸኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በቤንች ሸኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት ባለቤትነት በ2018 የበጀት ዘመን ሊያሰራ ላሰበው የቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ማሰራት ይፈልጋል።

1.     በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ 5/GC/BC እና ከዛ በላይ ፍቃድ ያላቸው።

2.     ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ እና ምስክር ወረቀት ዋናውን በማቅረብ በጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት የጨረታ ኮሚቴ የቢሮ ቁጥር 02 የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 1000 ብር በመክፈል መግዛት ይኖርባችኋል።

3.     የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና ከግብር ነፃ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

4.     የጨረታ ማስከበሪያ ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ጋራንቲ (ለ120 ቀናት የሚቆይ) ማቅረብ የሚችል።

5.     ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ በማቅረብ የፋይናንሻል እና የቴክኒካል ዶክመንቱን በጥቅሉ በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6.     እያንዳንዱ ፖስታ በተገቢው ሁኔታ በሰም ታሽጎ ማህተም መመታት እና መፈረም አለበት፡፡

7.     ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡

8.     እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፣ የተቋራጩ አድራሻ እና ስልክ/የተወካዩን ስልክ ቁጥር በመግለጽ መጻፍ አለበት፡፡

9.     ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ የፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው።

10. ጨረታው የሚታሸገው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት የጨረታ ኮሚቴ የቢሮ ቁጥር 02 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል፡፡

11. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት የጨረታ ኮሚቴ የቢሮ ቁጥር 02 ከሰዓት በኋላ 7፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

12. የሳይት ምልከታው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0917988437/0900635479

 

በቤንች ሸኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት

Save Tender