በአብክመ በባሕርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ኅ/ሥ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.የቅይጥ ማዳበሪያ ማምረቻ ጥሬ እቃ ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአሸናፊው መሸጥ ይፈልጋል፡፡
መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በባሕርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ኅ/ሥ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.የቅይጥ ማዳበሪያ ማምረቻ ጥሬ እቃ ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአሸናፊው መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. /C.P.O/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው።
3. በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣው ግልጽ ጨረታ በብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነፃ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (C.P.O) ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ከብ ማኅተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማኅተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላል፡፡
7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
9. ጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
11. አሸናፊው የአሸነፈውን ቅይጥ ማዳበሪያ የማምረቻ ጥሬ እቃ ሽያጭ በፍትሕ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል ይሸፍናል፡፡
12. የሚሸጠው ቅይጥ ማዳበሪያ ማምረቻ ጥሬ ዕቃ የሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ መጋዘን ሲሆን ጥራቱ የቅይጥ ማዳበሪያ ማምረቻነት የማይውል ሲሆን በአካል በማየት እንዲሞሉ እንዲሁም ቅይጥ ማዳበሪያ ማምረቻ ጥሬ እቃዎችን ለማንሳት የሚያስፈልጉ ማንኛውንም የወዛደር ማስጫኛ እና የትራንስፖርት ውጪ በመንገድ ላይ ያሉ ወጪዎች በአሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል፡፡ የቅይጥ ማዳበሪያ ማምረቻ ጥሬ እቃ ብዛት እና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል።
13. የቅይጥ ማዳበሪያ ሽያጭ እንዲሸጥ የሚፈለገው አብክመ ግብርና ቢሮ የመስተዳድር ምክር ቤቱን ውሳኔ ተጠቅሶ በቁጥር ግብ/ምቢ/ሐ/114/19 (በ19/05/2018 ዓ/ም በመመሪያው መሠረት እንዲወገድና በመወገድ የሚገኘው ገቢ በክልሉ ገንዘብ ቢሮ ገቢ እንዲደረግ ጠቅሶ በጻፈው መሠረት ሲሆን አሸናፊው ብር ገቢ የሚያደርገው በውሉ ላይ በምናሳውቀው በአብክመ ገንዘብና ኢኮኖሚ የሂሳብ ቁጥር መሆኑ ይታወቅ።
14. በዚህ ያልተጠቀሱ ሃሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ኅ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሠረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
15. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
16. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 18 08 26 26/09 11 59 05 34/ መጠየቅ ይቻላል፡:
የመርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃላ/የተ
