በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግንባታዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በጎፋ ዞን የዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
የ2ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም በወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በኩል 1ኛ ሸሌ ጤና ኬላ ግቢ ውስጥ ለሚገነባው የውሃ መስመር ዝርጋታ እና ደረቅ ቆሻሻ መጣያ ጉድጓድ ግንባታ 2ኛ. የላ ሻቦ ጤና ኬላ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚገነባው የውሃ መስመር ዝርጋታ እና የደረት ቆሻሻ መጣያ ጉድጓድ ግንባታ 3ኛ ቡኔ ጤና ኬላ ቅጥር ግቢ ለሚገነባው ደረቅ ቆሻሻ መጣያ ጉድጓድ ግንባታ 4ኛ. ኬንቾ ጤና ኬላ ቅጥር ግቢ ለሚገነባው የደረቅ ቆሻሻ መጣያ ጉድጓድ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
• በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• የግብር ከፋይነት ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• የዘመኑ ግብር የከፈለቡት መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
• የዘርፉ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
• ከዚህ በፊት በመንግሥትም ሆነ በግል በግንባታ ጥሩ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• ደረጃ 7/ሰባት እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
• የጨረታው ሠነድ የማይመለስ 500 ብር /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
• የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
• ዋጋውን ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ሞልታችሁ ማህተም ተደርጎ ተፈርሞበት በፖስታ ታሽጎ ኦርጅናልና ኮፒ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የመንግሥት የሥራ ቀናት በወረዳው ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
• ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
• ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
ማሳሰቢያ፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጎፋ ዞን የዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
