Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት
  • Address ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-42-90/91/
  • Website
  • Deadline12 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-12 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ 125CC እና 110 CC ጉልበት ያለው በቤኒዝል የሚሰራ ሞተር ሳይክል ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ 125CC እና 110 CC ጉልበት ያለው በቤኒዝል የሚሰራ ሞተር ሳይክል ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራች ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱ ሁኔታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

1.     ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

3.     የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ CPO 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው።

4.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር ብቻ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000342552424 በመክፈል

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ኮፒ ይዞ በመቅረብ ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ምድር ቤት በሚገኝ ቢሮ ቀርበው ሰነዱን ማግኘት ይቻላል።

ለጨረታው የሚቀርበውን የሞተር ሳይክሉን ይዘትና ዓይነት የሚያሳይን ፎቶ ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

5.     የጨረታ ሰነዱ በተጫራች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ ማድረግ በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተውና በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት 9፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል።

7.     የጨረታ አሸናፊ ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ሲዳማ ብ/ክ/ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ በማቅረብ ያስረክባል።

በተጨማሪም አሸናፊ ድርጅት አስቀድሞ የዕቃውን ናሙና ማቅረብና ማሳየት ከቢሮው ጋር መተማመን ይኖርበታል፡፡

8.     ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል።

–       ዝርዝር የጨረታ ሂደት በጨረታው ሰነድ መመሪያ ላይ ተገልጿል።

–       ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ 046-212-4290/91

 

የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት

Save Tender