Tender Detail

Tender Details

  • Company የጨና ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa, Phone: 0473380173
  • Website
  • Deadline02 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-02 00:00:00
  • Categories Construction Works

የጨና ወረዳ ግብርና አካ/ጥ/ህ/ሥራ/ል/ጽ/ቤት በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ ባላሻሻ ቀበሌ ማዕከል ላይ ለሚገነባው የመጀመሪያ ደረጃ የቁም የእንስሳት ግብይት ማዕከል ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

የጨና ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2

የጨረታ ማጣቀሻ ቁጥር ET-SWEPR-461208-CW-RFQ/የጨና ወረዳ ባሳሻሻ ቀበሌ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታ

የጨና ወረዳ ግብርና አካ/ጥ/ህ/ሥራ/ል/ጽ/ቤት በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ ባላሻሻ ቀበሌ ማዕከል ላይ ለሚገነባው የመጀመሪያ ደረጃ የቁም የእንስሳት ግብይት ማዕከል ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ የጨና ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ይህን ተከትሎ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከዚህን በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች ሟሟላት ያለባቸው መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል

1. የታደሰ የ2018 ዓ.ም ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

2. የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል

3. የንግድ ምዝገባ /tin number/ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

4. የብቃት ማረጋገጫ የምስከር ወረቀት (የኮንትራክተሮች ምዝገባ የምስክርወረቀት) ከሚመለከተው አካል (ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር/ተጠያቂው ከልል ቢሮ) ማቅረብ የሚችል/የምትችል

5. GC/BC ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

6. በግዥና ንብረት አስተዳደር ስር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባችሁ ከምዝገባና አስተዳደር ኤጀንሲ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል

7. ሳይት ቪዝት/Visiting the project site/ ስለማድረጋቸው ተጨባጭ መረጃ ከጨና ወረዳ ግብርና አካ/ጥ/ህ/ሥ/ል/ጽ/ቤት ማምጣት የሚችል/የምትችል

8. ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ለተጨማሪ መረጃ ከጨና ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ ዘውትር በሥራ ሰዓት መግዛት ትችላላችሁ፤

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጨና ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፣

10.ተጫራቾች የጨረታው ዶክመንት አንድ(1) ቴከኒካል ኦርጅናል እና ሁለት ቴከኒካል ኮፒ አንድ(1) ፋይናንሻል ኦርጅናልና ሁለት ፋይናንሻል ኮፒ የጨረታ ዶከመንት በአንድ አንድ ፖስታ ለየብቻ በማሸግ ከተጨማሪ ቴከኒካልና ፋይናንሻል ሁለት ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕና የጨረታ ማስከበሪያን ጨምሮ በእናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

11.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 300,000(ሦስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ(Cpo) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣

12. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ ይቆያል ፡፡

13. ጨረታው በ31ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል፡፡ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሰነድ የመክፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም ፡፡

14.የጨረታ መዝጊያና መከፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይሰዓት ይሆናል፡፡

15.ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን ከምትገዙት የጨረታ ቴከኒካል ዶክመንት ላይ ማየት ይቻላል

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0473380173/174 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል::

የጨና ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender