Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የጎዴ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address Addis Ababa, Phone: 0118668072
  • Website
  • Deadline09 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-09 00:00:00
  • Categories Machinery , Cloth And Shoes , Office Equipment

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የጎዴ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሎት 01 እስከ ሎት 04 ድረስ ያሉት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የጎዴ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የጎዴ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሎት 01 እስከ ሎት 04 ድረስ ያሉት ዕቃዎች -

1.የደንብ ልብስ 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች 3. አላቂ የሕከምና እቃዎች 4. ለፕላንት ማሽነሪ እድሳት ጥገና በጨረታው ለመወዳደር ለምትፈልጉ

1.ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡

2.በገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው እቃና አገልግሎት ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፡፡

3.ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡

4.ተጫራቹ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን ዓይነት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ በተከታታይ አስር የስራ ቀን በስራ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የጎዴ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡

5.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበት በሲ.ፒ.ኦ. ብር የአንድ ሎት 2000(ሁለት ሺ ብር) የጨረታ ሰነዱን ሲያስገባ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚጫረቱበትን ዋጋ እስከ ነቫቱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7.ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ክፍት ነው፡፡ በዘኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8.አሸናፊዎች በጨረታው አሸናፊነት ከተገለፀው ቀን ከ7ኛው ቀን በኋላ መልካም አስተሳሰብ ዋስትና 10 ፐርሰንት በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል በመፈፀም ያሸነፉበትን እቃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

9.መሥሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በመከፈል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡

10.እያንዳንዱ ተጫራች የሚያስገባቸውን እቃዎች ሳምፕል ሲያመጡ በፎቶ የሚያስፈልጉትን እቃዎች ማምጣት ይኖርበታል፡፡ ማንኛውም ድርጅት ናሙና ላይ ስልከ ቁጥር ወይም የድርጅቱ ማህተም ከተደረገ ውድቅ ይሆናል፡፡

አድራሻ ፡-የካ አባዶ ወረዳ 14 ፖሲስ ጣቢያ ጀርባ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- /0118668072/

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ት/ት መምሪያ

Save Tender