በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክ/ከተማ የሚገኝ ለአከባቢ ጥበቃ ላብራቶሪ ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የላብራቶሪ ዕቃዎችን (Equipment) በጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የኦሮሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
የላብራቶሪ ዕቃዎች ጥገና ግልፅ የግዥ
ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክ/ከተማ የሚገኝ ለአከባቢ ጥበቃ ላብራቶሪ ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የላብራቶሪ ዕቃዎችን (Equipment) በጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥንና የፋይናንስ መመሪያዎችን የምታማሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጸለን።
1. 1 በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ለተጨማሪ እሴት ታክሰ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
3. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. 4, የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እና የማይመለስ ብር 100 (መቶ) በመክፈል የኦሮሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 የግዥና ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
6. የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ unconditional Bank grant or ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ብቻ በማቅረብ ተጫራቹ የዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ) ማስያዝ ይኖርበታል።
7. ተጫራቾች የጥገና ዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ለውድድር በሚያቀረቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማሰፈርና ማህተም ማድረግ ፤የጨረታ መወዳደሪያ ዶክመንት
7.1. የቴክንክ ዶክመንት ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በተለያየ ፖስታ መቅረብ ይኖርበታል።
7.2. የፋይናንስ ዶክመንት ኦሪጂናልና ኮፒ ለየብቻ በተለያየ ፖስታ መቅረብ ይኖርበታል።
8. ፖስታ ላይ የዶክመንቱን አይነት ማለትም ኦሪጅናል ወይም ኮፒ የሚል ፅሁፍ በመፀፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋዜጠ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ የስራ ቀናት 06/06/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
10. 10 የጨረታው አሸናፊ በራሱ ወጪ ዕቃዎቹን የመ/ቤቱ ንብረት ከፍል ገቢ ማድረግ አለበት።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118349814 ወይም 0900082882/ 0982146539 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መ/ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር
የኦሮሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
