Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916839798
  • Website
  • Deadline07 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-09 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Electronics Materials

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት-1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ሎት-2 የሞተር ሳይክል

•        ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

•        የዕቃው አቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

•        የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

•        ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የዕቃዎቹን እስፔስፊኬሽን በተገለፀው መሰረት ተሞልቶ እንዲገለጽና ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የም/ጉ/ዞ/ፋ መምሪያ በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን፡፡

•        ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 10,000 /አስር ሺህ/ እና ለሎት 2 ብር 10,000 /አስር ሺህ/ ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

•        ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጁት ዝርዝር አስፔስፊኬሽን ላይ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

•        የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡

•        አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን የምስ/ጉ/ዞን ፋይናንስ ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡

•        መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

•        ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0916839798 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

Save Tender