የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ ካፒታል ቤት የብሬል መጻሕፍትን ለማሳተም የህትመት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Central Ethiopia Region Bureau of Education (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ-003
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ ካፒታል ቤት የብሬል መጻሕፍትን ለማሳተም የህትመት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
መስፈርት
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እንደዚሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ አንድ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 001 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000 ብር (ሠላሣ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ወራቤ ከተማ ክልል ትምህርት ቢሮ ግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
7. የውል ማስከበሪያ: የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሽነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ7 ቀናት በኋላ ውሉን መፈረምና የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና አይነቶች ክፍያ በሚፈፀምበት የገንዘብ አይነት የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ አለበት፡፡
8. ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጨረታው ውድድር በአሸናፊው የተሰጠው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
9. ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጨረታው ውድድር በአሸናፊው የተሰጠው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
10. ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከተፈረመ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይመጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጨረታው ውድድር በአሸናፊው የተሰጠው ዋጋ ሳይቀየርእስከ 25% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
11. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የብሬል ህትመት ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡
12. የጨረታ ሰነዱ ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ብቻ ነው።
13. መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-771-06-88 መደወል ይችላሉ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ
