አሙግ አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ለሚያሠራው ሕንጻ ኮንትራክተር በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።
አሙግ አክስዮን ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
አሙግ አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ለሚያሠራው ሕንጻ ኮንትራክተር መቅጠር አስፈልጎታል። በመሆኑም የስትራክቸርና የፓርቲሽን ሥራዎችን ለመሥራት ከደረጃ 6 በላይ ፈቃድ ያላችሁ የሕንጻ ተቋራጮች የሚከተሉትን ሥራዎች ለመሥራት ዋጋ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል።
በዚህም መሠረት፡-
• የፎርም ዎርክ ስራ (የሰው ኃይል ከእቃ አቅርቦት ጋር)
• የብረት ስራ (የሰው ሀይል ብቻ)
• የኮንክሪት ሙሌት ስራ (የሰው ሀይል ብቻ)
• የፓርቲሽን (የብሎኬት ግንባታ እና የልስን) ስራ (የሰው ሀይል ብቻ)
• የጣሪያ ስራ (የሰው ሀይል ብቻ)
ከላይ የተጠቀሰውን ሥራ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ሠነዶች በማህበሩ ጽ/ቤት እንድታቀርቡ እናሳስባለን።
1. ተወዳዳሪዎች በተመሳሳይ ሥራ ከዚህ በፊት የሠሯቸውን ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ዝርዝር ከአድራሻ እና የመልካም አፈጻጸም ደብዳቤ (Reference) ጋራ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተወዳዳሪዎች ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ ተጨማሪ አሴት ታክስ ሰርተፍኬት (VAT)፣ የብቃት ማረጋገጫ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ ይኖርበታል።
3. ተወዳዳሪዎች ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች በተጨማሪ በBC/GC 6 ደረጃና ከዛ በላይ የተመዘገበ መሆን አለባቸው።
4. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 1,000 ብር (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በመ/ቤታችን ማግኘት ይችላሉ።
5. ተወዳዳሪዎች 20,000 ብር (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስያዣ (CPO) ማቅረብ አለባቸው።
6. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሠነድ በመሙላት ፋይናንሺያል ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻው፣ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ኮፒ በአንድ ላይ እና (CPO) ለብቻው፣ በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ በሁሉም ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተም ተመቶበት መቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል ለመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
8. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ከጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመ/ቤቱ ከጠዋት 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ። ጨረታው እስከ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ድረስ ተከፍቶ ይቆያል፣ ከዚያ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
9. ጨረታው ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ይከፈታል።
10. አሙግ አ.ማ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ አሜሪካን ግቢ ከዋጄዲ ህንጻ ወረድ ብሎ፣ ስልክ ቁጥር 09116009361 ድን
• አድራሻ አሜሪካን ግቢ ከዋጂዲ ሕንጻ ወረድ ብሎ፣ ስልክ ቁጥር 09 11 60 09 36 ፣ 09 11 11 75 37፣ 09 11 22 11 05
አሙግ አክስዮን ማህበር
