የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
· ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት መወዳደሪያ ኤንቨሎፕ ውስጥ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
· የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ከግዥ ፋይናንስና ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
· የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 05 ከ1፡30 እስከ 11፡30 ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል።
· ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሣሣይ ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
· ተጫራቾች ብር 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ዶክመንቱ ሲከፈት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
· የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት። በተጨማሪ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው በሁለት ኮፒ መቅረብ አለባቸው።
· ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን እቃ የግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በእስፔስፊኬሽኑ እና በናሙናው መሠረት በ30 ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በሚገኝበት መጋዘን አቅርቦ ማስረከብ አለበት።
· በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ወይም ሳምፕል ወጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም፡፡
· የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈው ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ መስጠት የሚችል፡፡
· በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆን በመንግሥት ግዢ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።
· ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡
· ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቀበሌ 03 ድሬዳዋ
ስልክ ቁጥር፡- 025 112 48 92
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
