Tender Detail

Tender Details

  • Company በማ/ኢ/ክ/መ/ በከምባታ ዞን የዳምቦያ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት
  • Address ከምባታ ዞን ዳምቦያ ወረዳ: በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ , Phone: 0916 39 12 35
  • Website
  • Deadline09 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-09 00:00:00
  • Categories Construction Works

በማ/ኢ/ክ/መ/ በከምባታ ዞን የዳምቦያ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በዋን ዋሽ በጀት ድጋፍ ከተያዘው ለት/ቤቶች እና ለጤና ጣቢያዎች የግንባታ ስራዎችን በተለያዩ ሎቶች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በማ/ኢ/ክ/መ/ በከምባታ ዞን የዳምቦያ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ደወፋ 0003

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማ/ኢ/ክ/መ/ በከምባታ ዞን የዳምቦያ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በዋን ዋሽ በጀት ድጋፍ ከተያዘው ለት/ቤቶች እና ለጤና ጣቢያዎች የግንባታ ስራዎችን በተለያዩ ሎቶች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

የትምህርት ፡- ሎት -1

(1.1) ዱሜ ለመቻ 1ኛ/ ደረጃ ት/ቤት የውሃ መስፋፊያ ሥራ

የትምህርት ፡- ሎት - 2

(2.1) በሃንጀ ላሎአሞ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች ንጽህና መጠበበቂያ ግንባታ ስራ /MHM/

(2.2) ዱሜ ለመቻ 1ኛ ደረጀ ት/ቤት የወንዶች ዘመናዊ አዲስ ሽንት ቤት ግንባታ ሥራ

የጤና፡- ሎት -1

(1.1) ለመገሬ ጤና ጣቢያ የውሃ ማሰባሰቢያ 10,000 ሊትር ሮቶ ማስቀመጫ ግንባታ ሥራ

(1.2) ለጌንዴለ ጤና ኬላ አዲስ ሻወር ቤት ግንባታ ሥራ

(1.3) ለወንዶ ጤና ጣቢያ የውሃ ማሰባሰቢያ 10,000 እና 5,000 ሊትር ሮቶ ማስቀመጫ ግንባታ ሥራ

የጤና ፡ ሎት 2

(2.1) ለዶንቆርቾ ጤና ኬላ እንስኔተር ግንባታ ሥራ

(2.2) ለጌፌጤ ጤና ኬላ እንስኔትር ግንባታ ሥራ

(2.3) ለ ሀዳራ ጤና ኬላ አዲስ ሽንት ቤት ግንባታ ስራ

በመሆኑም፡-

1.     የዘመኑ የ2018 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው

2.     የግብር ከፍይነት መለያ ቁጥር ያለው

3.     የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው

4.     የቫት ተመዝጋቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው

5.     የመንግስት ግዥ አቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት በኦንላይን /online/ ያለው

6.     በግብር ዓመቱ ተገቢውን የታክስ እና የግብር ግዴታ የተወጣ መሆኑን የሚያሳይ ክሊራንስ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል

7.     የጨረታ ማስከበሪያ በየዘርፉ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ በጥሬ/ በባንክ በተረገጋጠው ሲፒኦ (cpo) ማቅረብ የሚችል

8.      ደረጃ 5/(GC) እና ከዚያ በላይ

9.      ለትምህርት ሎት-1 ብቻ ደረጃ 5/wwc/ ያለው

10. የሳይት ምልከታ የምስክር ወረቀት ከአሰሪው መ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል።

11. ጨረታው ከተከፈተ ለ15 ቀናት ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ይሆናል።

12. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ እና የድርጅቱን ማኅተምና ስም ማሳረፍ በተጨማሪ የተወዳደሩበትን ሎቶችን ለይቶ መጥቀስ ይኖርበታል።

13. ከ2017 ዓ/ም ጀምሮ ያለው መልካም ስራ አፈጻጸም 3 እና ከዚያ በላይ በየዘርፉ ማቅረብ የሚችል።

14. ሁሉንም ፖስታ በእናት ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማስገበት ይጠበቅበታል።

15. የ2018 ዓ/ም በዘርፉ የተደሰ ሙያ ፈቃድ ያለው።

ከተራ ቁጥር 1-15 የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ተጫራች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ በ20 ቀናት ውስጥ የስራውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከ ዳ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 03 የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ዋጋውን በአንድ ኦርጅናል እና በሁለት ኮፒ በግሉ በታሸገ ፖስታ በማድረግ እና ቴክኒኩን ለብቻ በማሸግ በዳ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 21ኛው ቀን 7፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ21ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን 7፡30 ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 21ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቹ ወይም ተወካዩ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉልም።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ተጫራች ከአንድ ሎት ውጪ ሌላ መግዛት አይችልም።

ለበለጠ መረጃ፡- 0916 39 12 35/0945 88 33 71

 

ከዳ/ወ/ፋይ/ጽ/ቤት

Save Tender