Tender Detail

Tender Details

  • Deadline09 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price700.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-09 00:00:00
  • Categories Vehicle

የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን፣ የአፍሪካ ልህቀት አመራር አካዳሚ፣ የፌዴ


ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር PPS/VP-16FB/05/04/2018

የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን፣ የአፍሪካ ልህቀት አመራር አካዳሚ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የአርዳይታ የግብርና ቴክኒከና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ፣ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡

1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡

2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንከ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ ገቢ በማድረግና ያስገቡበትን የባንክስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡

4, ተጫራቶች ለሚገዙት ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 5% (እምስት በመቶ) ነገር ግን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር ያልበለጠ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡

5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፡፡ ይሁንና የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 5% (ለምስት በመቶ) ነገር ግን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር ያልበለጠ ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

6. ተሸከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ ዕዳ ካለበት በባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ሲሆን የጉምሩክ ቀረጥ ግብር አዳ፣ የስም ማዛወሪያ፡ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው የሚሸፈን ይሆናል፡፡

7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይክፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት እያስቀረውም፡፡

8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ከፍያውን በተጠቀስው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል::

9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች ያሸነፉባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ማስያዝ አለባቸው::

10. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡

11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ተሽከርካሪውን በo (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው::

12. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ፡- የተቋማችንን ድህረ-ገጽ www.pps.gov.et ይጎብኙ

የፌደራል መንግሥት ግዥ አገልግሎት

Save Tender