Tender Detail

Tender Details

  • Company የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 222 14 79
  • Website
  • Deadline07 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-07 00:00:00
  • Categories Other

ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ለዙሀሙሲት መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸው ፊልተር ማቴርያሎችን ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC09/2018 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር


የጨረታ ጥሪ

ግዥ ፈጻሚ አካል ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን

ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር NCB WWC 09 /2018

ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ለዙሀሙሲት መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸው ፊልተር ማቴርያሎችን ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC09/2018 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር/ዓይነት Summery of goods

መለኪያ

 

ብዛት

 

ምርመራ

 

የተለያዩ መጠን ያላቸው ፊልተር ማቴርያሎች በአይነት/ Items/ ብዛት 8

M3

 

3100.96

 

All are silica sand type

 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው

እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN ፤ የቫት ምዝገባ የምስከር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ 60 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 600,000 (ስድስት መቶ ሺህ ብር) በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡

3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ኮርፖሬሽን ዋናው መስሪያ ቤት ከገንዘብ ያዥ ፋይናንስ ዳይሮክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ማሰተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ነጋ ቦንገር ሆቴል በስተ ምዕራብ 100 ሜትር ገባ ብሎ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን (የዋጋ ሰነዳቸውን) በጥንቃቄ ከሞሉ በኃላ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20(ሃያ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህርዳር ከተማ በውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ በግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 25 ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 20 ኛው ቀን ከቀነ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ቀነ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡

6.ተወዳሪዎች የሚወዳደረበትን ጨረታ ሳምፕል⁄ ናሙና⁄ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ለእያንዳንዱ አቅርቦቶች ስሙን በመግለጽ እስከ 0.5 ኪሎግራም ለየብቻ አሽጎ በማቅረብ የቀረበው ናሙና ስምና ዲያሜትር ታይቶ ትክከል ነው ተብሎ ሲታመን ብቻ የዋጋው ማቅረቢያ ፖስታ ይከፈታል፣ በመጨረሻም አሸናፊ ድርጅት ውል ይዞ የሚያቀርበው አቅርቦት ናሙና ምርመራ ተሰርቶ ማለፉ ከተረጋገጠ በኋላ እርክክብ ይፈጸማል፡፡

7. የአቅርቦቱ ትራንስፖርት በተመለከተ ተጨራቹ በራሱ የትራንስፖርት እና በኮርፖሬቱ ተሸከርካሪ የሚቀርብበትን ዋጋ በመጨራቻ ሰነዱ ላይ መሙላት ይጠበቅበታል፡፡

8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በ ግዥ እና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ ፣ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰነድ ግዥ መፈፀም እንጅ ፖስታውን ማሰገባት የሚቻለው ባህር ዳር ከተማ ዋናው መስሪያ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ:-

መስሪያ ቤት ፡ የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዳግማዊ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት

ፖ.ሳ.ቁ(106) ፡ ስልክ ቁጥር [0582221479]

ባህር ዳር

ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender